የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የመጪዉ የአዲስ አመት በአል አስመልክቶ የበዓሉን የገበያ አቅርቦትና የንግድ እንቅስቃሴ ዝግጅት ዙሪያ በዛሬዉ እለት መግለጫ ሰጥቷል።
የቢሮዉ ሃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አዲስ ዓመት በዓል በማስመልከት የሚፈጠረውን የኅብረተሰብ ከፍተኛ የመሰረታዊ ፍጆታ ምርቶች ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ሰፊ የዝግጅት፣ የአቅርቦትና የቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በበአሉ ከቄራ እንስሳት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዶሮዎች እና ከ42.7 ሚሊዮን በላይ እንቁላል ለገበያ እንደሚቀርቡ ተጠቅሷል።
ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ በግና ፍየል እንዲሁም 62 ሺህ 600 ደረቅ ከብቶች ለበዓሉ ገበያ እንደሚቀርቡ የከተማዋ ንግድ ቢሮ ተናግሯል።
ለበዓሉ ገበያ
7መቶ 8ሺህ 266 ኩንታል ቀይ ሽንኩርት
እንደሚቀርብ የተናገሩት የቢሮዉ ሀላፊ ሀቢባ ሲራጅ ፤ 227 ሺህ 8 መቶ 85 ኩንታል የጤፍ ምርት ለማቅረብ መታቀዱን በመግለጫቸው ገልፀዋል።
ከ3.7 ሚሊዮን ሊትር በላይ ፈሳሽ የምግብ ዘይት ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ ዝግጅት መጠናቀቁን የቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃላፊ ሀቢባ ሲራጅ ተናግረዋል።
ለህብረተሰቡ በጥራትና በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ ሲባል የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የፋብሪካ ምርቶች መሸጫ ማዕከላት አገልግሎቱ እንዲሰጡ ይደረጋል ተብሏል።
5 የቀንድ እንስሳት መሸጫ ማዕከላት እና 2መቶ 64 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በሳምንቱ ሙሉ ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ መወሰኑን ሀላፊዋ ጠቁመዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
