የኢትዮጵያ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
በ 2019 የሚከበሩ ብሔራዊ ሀይማኖታዊና የአደባባይ በአላት አከባበርን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የህዝብ ክብረ _ በዓላትን በማጎልበት ብሔራዊ አንድነትንና ልማትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጿል ።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ነፊሳ አልመሃዲ እንደገለጹት በ2019 በጀት ዓመት በሀገሪቱ ህዝቦች ዘንድ የሚታወቁ የህዝብ ክብረ በዓላትን በማልማትና በማስተዋወቅ ባህል በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲዳብር ከማድረግ ባሻገር የጋራ እና የተናጥል እሴቶችን በማጉላት የመደጋገፍ፣ የመተባበር እና የአብሮነት መንፈስ እንዲጎልብት ብሎም ሀገራዊ አንድነት እንዲጠናከር እየተደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ ይህን ልዩ ባህላዊ ሀብትዋን ለማልማት እና ለማበረታታት ብሔራዊ የባህል ልማት ፖሊሲን ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ በመግለጫው ተገልጿል ።
በ2018 በጀት ዓመት ብቻ፣ ለሦስት ወራት የቆየ የባህል ንቅናቄ በማድረግ 46 ሚሊዮን ህዝብን በማሳተፍ ባህላዊ እሴቶችንና አገር በቀል እውቀቶችን ማጉላት መቻሉን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልመሃ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የህዝብ ክብረ በዓላት በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው እና የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለው ገልጸዋል ።
ሰላማዊት ዲታ
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም
