በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የአበባ ምርት በስፋት እየተካሄደባቸው ያሉ ምቹ አካባቢዎች መኖራቸውን የተገለጸው ሲሆን በመቀሌ እና ድሬዳዋ ከተሞች ግን መቀዛቀዝ እንደታየባቸዉ ተገልጿል።
ኢትዮ ኤፌም ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ አበባ ፥ ፍራፍሬ እና አትክልት አምራቾች ማህበር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቴዎድሮስ ዘዉዴ እንደሚሉት አዳዲስ የአበባ ምርት ኢንቨስትመንት ሀኔታዎች መኖራቸውን ይገልጻል።
ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲገቡ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነዉ ያሉት አቶ ቴዎድሮስ መቀሌ ላይ ብዙም እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልፀዋል በተመሳሳይ መልኩ ድሬዳዋ ከተማ አበባን በተመለከተ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እንዳለ ተናግረዋል።
በባቱ ፣ቢሾፍቱ ፥ሆለታ እና ሰበታ ሰፋፊ የአበባ እርሻ የሚካሄድባቸው መሆኑን ያነሱት የማህበሩ ዳይሬክተር በባህርዳር ዙሪያ አየር መንገዱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸዉን እና ለዉጪ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ያሉ ኩባንያዎች መኖራቸዉን ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በጉራጌ ዞን አካባቢ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መሬቶች መኖራቸዉን ተለይቶ ሂደቶች መጀመራቸውን አቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በሀዋሳ ከ100 ሄክታር በላይ የአበባ እርሻ የሚገኝበት አካባቢ መሆኑ ተጠቅሷል።
የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ የአበባ ምርት ከሌሎች የሆልቲካልቸር ምርቶች በገዘፈ መልኩ እድገቱ መሻሻሎች እንደታየበት መሆኑን ጠቅሰዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሎጀስቲክ አቅሙን ከፍ ማድረጉን ተከትሎ ለምርቱ ተፎካካሪነት እድል ፈጥሯል ሲሉም ይገልፃሉ።
ቁምነገር አየለ
ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም
