የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከኢራን ጋር «የኑክሌር ስምምነት ላይደረስ ይችላል» አሉ


በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው የሃይል እርምጃ በተባባሰበት በዚህ ወቅት፣ የአሜሪካ የኢነርጂ ሚኒስትር ክሪስ ራይት ከኢራን ጋር የኑክሌር ስምምነት የመፈራረም እድሉ አነስተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ሚኒስትሩ እሁድ ዕለት ከኤቢሲ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ አሜሪካ ስምምነት ከማድረግ ይልቅ የኢራንን የኑክሌር መሰረተ ልማት እና አቅም በወታደራዊ ድብደባ ወደ ማፍረስ ልታደላ እንደምትችል ጠቁመዋል።
 
ኢራን የኑክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሆነ ትገልጻለች፣ አሜሪካ ግን የኢራንን የኑክሌር እና የሜሳይል ማምረት አቅም እያዳከመች እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
 
አክለውም ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ የሚቻለው ወደፊት በሚመጣው አዲስ የኢራን አስተዳደር ወቅት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። ይህም የትራምፕ አስተዳደር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ስምምነት ለማድረግ ያለው ተስፋ እየመነመነ መምጣቱን ያሳያል።

ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *