ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካናዳው አውሮፕላን አምራች ቦምባርዲየር በአሜሪካ ውስጥ አውሮፕላኖችን ካላመረተ በስተቀር ኩባንያው በአሜሪካ የሚያደርገውን ሽያጭ እንደሚያግዱ ዝተዋል።
ቁጣ የተቀላቀለበት የማህበራዊ ሚዲያ ፅሁፋቸዉ፤የአሜሪካው መሪ በሺዎች የሚቆጠሩ አውሮፕላኖቹ በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ አየር መንገዶች የሀገር ውስጥ በረራዎች ላይ በሚገኙት በዚህ አምራች ላይ፣ በዚህ ዓመት ውስጥ የወሰዱት ሁለተኛው እርምጃ ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡
ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ፤‹‹ከእንግዲህ ቦምባርዲየር በአሜሪካ ውስጥ አይሸጥም››በማለት የለጠፉ ሲሆን፤ሽያጩን እንዴት እንደሚያቆሙ ግን በዝርዝር አልገለጹም።
ገበያችንን ከፈለጉ እዚህ መገንባት አለባቸው፤ አሜሪካን እንደ ‹‹ካዝና›› ማየታቸውን ማቆም አለባቸው ብለዋል።
ትራምፕ አክለውም፤ ካናዳ ታላላቅ የአሜሪካ ባንኮቻችንን እና ኩባንያዎቻችንን እዚያ እንዳይሰሩ ትከለክላለች ካሉ በኋላ፣ ያ ዘመን አብቅቷል ብለዋል።
እንደ ትራምፕ ገለጻ የአሜሪካ ገበያ ለቦምባርዲየር ጠቅላላ ገቢ ከግማሽ በላይ ድርሻ አለው።
ቦምባርዲየር በሰጠው መግለጫ፤በአሜሪካ ውስጥ ባለው እየተስፋፋ ያለ እንቅስቃሴ እንዲሁም በ47 ግዛቶች ውስጥ ከሚገኙ ወደ 2 ሺህ 8መቶ በሚጠጉ የአሜሪካ ኩባንያዎች በተውጣጣው የአቅርቦት ሰንሰለቱ አማካኝነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስራዎችን በአሜሪካ ውስጥ እየፈጠረ መሆኑን ገልጿል።
የካናዳው ኮርፖሬሽን አክሎም፤አውሮፕላኖቹ የሚገነቡት እንደ ሞተር እና አቪዮኒክስ ባሉ ታላላቅ የአሜሪካ ኩባንያዎች በሚቀርቡ ግብዓቶች መሆኑን ገልጾ፤ በዚህ ዓመት መጨረሻ በፎርት ዌይን፣ ኢንዲያና አዲስ ፋብሪካ ለመክፈት ማቀዱን አስታውቋል።
እስከዳር ግርማ
ጳጉሜ 03/2018 ዓ.ም
