በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ በዛሬው እለትተጀምሯል።

በከተማ አስተዳደሩ ከ1.3 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በ2019 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመከታተል የተመዘገቡ ሲሆን በአዲሱ የትምህርት አመት ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተማሪዎችን ውጤትና እና ሥነ ምግባር ለማላቅ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራቱን ተመላክተዋል።

ቢሮ ው እንደገለጸው በትምህርት ዘመኑ ለተማሪዎች በቂ ደንብልብሶችን ጨምሮ ደብተሮችና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶች ዝግጁ ከመደረጋቸው ባሻገር የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ጥራቱን ጠብቆ ለተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጧል፡፡

የትምህርት አመቱ ፍጹም ሰላማዊና ተማሪዎች ውጤታማ የሚሆኑበት አመት እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪ ቢሮው ጥሪውን አቅርበዋል።

ለዓለም አሰፋ

መስከረም 5/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *