የፔንታጎን ዋና ተቆጣጣሪ ከየካቲት 28 እስከ ሰኔ 30፣ 2026 ዓ.ም. የተካሄደውን “Operation Epic Fury” የተሰኘ ወታደራዊ ዘመቻ በተመለከተ ባወጣው ይፋዊ ሪፖርት፣ አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት ከዚህ ቀደም ይፋ ከተደረገው እጅግ የላቀ ከባድ ኪሳራ እንደደረሰባት አጋልጧል።
እንደ መረጃው ከሆነ በሰው ሕይወትና አካል ጉዳት በኩል ቢያንስ 18 የአሜሪካ ወታደሮች ሲገደሉ (11 በውጊያ፣ 7 ከውጊያ ውጭ)፣ 417 ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል።
ሲቢኤስ (CBS) ባወጣው ዘገባ በቁሳቁስና በአውሮፕላኖች ላይ የደረሰው ውድመት ቀላል የሚባል አይደለም። 30 የ-MQ-9 Reaper ድሮኖች፣ 4 F-15E ተዋጊ ጄቶች፣ 1 F-35A Stealth ጄት እንዲሁም A-10፣ KC-135፣ HH-60W እና Apache ሄሊኮፕተሮች ወድመዋል፤ ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በተጨማሪም ኢራን “Dive-LD” የተባለ የውኃ ውስጥ ሰርጓጅ መንኮራኩር መማረኳን ገልጻለች።
በኩዌት፣ ባህሬን፣ ኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራቅ፣ ኦማን እና ዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎችና መሠረተ ልማቶች ወድመዋል።
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ባወጣው በዚህ ሪፖርት፣ ከየካቲት እስከ ሰኔ ድረስ በኢራን ላይ በተካሄደው ዘመቻ አጠቃላይ 33.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ መደረጉንና ከዚህ ውስጥም 22.3 ቢሊዮን ዶላሩ ለተተኳሾችና ለጦር መሣሪያዎች የዋለ መሆኑን አስታውቋል። ሪፖርቱ አክሎም ዘመቻው “በወሳኝ የጦር መሣሪያ ክምችቶች ላይ እጥረት አስከትሎ፣ ለተተኳሽና ለመሣሪያ አቅርቦት ያለውን የኢንዱስትሪ መሠረተ ልማት ውስንነት አጋልጧል” ብሏል።
ይህ ሪፖርት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ምንም የጎላ ጉዳት አልደረሰብንም፣ በቂ የመሣሪያ ክምችት አለን” ሲሉ የሰጡትን ተደጋጋሚ ማስተባበያ የሚቃረን ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አገራት በከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ መቃቃር ውስጥ ይገኛሉ። አሁንም ቢሆን ወሳኙ የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተዘግቷል።
አዲስዓለም አበበ
መስከረም 6/2019 ዓ.ም
የፔንታጎን ይፋዊ ሪፖርት እና አሜሪካ ኢራን ውስጥ የገጠማት አስደንጋጭ ኪሳራ
