“ዓለም በAI ምክንያት ቢሰጋ ትክክል ነው፤ ነገር ግን እኛን ማመን አለበት» – የኦፕን ኤአይ መሪ

የቻትጂፒቲ (ChatGPT) አዘጋጅ ኦፕን ኤአይ የበላይ ኃላፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስጋቶች እየጨመሩ በሄዱበት በዚህ ወቅት ህዝቡ እርሳቸው በሚመሩትና መሰል ኩባንያዎች ላይ የበለጠ እምነት ሊኖረው እንደሚገባ ተግረዋል።

ሳም ኦልትማን በማክሰኞ ዕለት በሳን ፍራንሲስኮ በተካሄደ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ “ዓለም እኛ ትክክለኛውን ነገር እንደምናደርግ ማመን አለበት፤ ምክንያቱም ትክክለኛው መንገድ እሱ በመሆኑና የነገሩን አደገኛነትና ክብደት ስለምንረዳው ነው” ብለዋል።

ሆኖም ኦልትማን የቴክኖሎጂዎቹ አቅም በፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ሰዎች ስጋት ቢገባቸው ተገቢ መሆኑንም አምነዋል።

በሌላ በኩል በዋሽንግተን ንግግር ያደረጉት ሴናተር በርኒ ሳንደርስ እና የቀድሞው የትራምፕ አማካሪ ስቲቭ ባነን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ጥብቅ የመንግስት ቁጥጥር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የኦልትማን አስተያየት የመጣው ሴልስፎርስ (Salesforce) የተሰኘው የሶፍትዌር ኩባንያ ባዘጋጀው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

እርሳቸውም ሲናገሩ “ነገሮች እንዴት መስመር ሊስቱ እንደሚችሉ ለመገመት አሁን ላይ ብዙ ምናብ አይጠይቅም” ሲሉ ገልጸው፤ “ዓለም በዚህ ነገር ቢሰጋና ቢፈራ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።

ይህ ንግግራቸው ባለፈው ሳምንት ከአንትሮፒክ (Anthropic) የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኩባንያ የለቀቁ አንድ ተመራማሪ ያስተላለፉት መልእክት በይነመረብ ላይ ከተሰራጨ በኋላ የተሠጠ ነው።

ተመራማሪው AI ያለ ቁጥጥር ከተተው እስከ አስረኛው ክፍለ ዘመን ማጠቃለያ (በዚህ አስር ዓመት ውስጥ) የሰውን ልጅ በሙሉ ሊያጠፋ ይችላል ሲሉ አስጠነቅቀው ነበር።

ሀና ሰይፉ

መስከረም 6/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *