መስከረም 22 ቀን በግዮን ሆቴል የኢሬቻ ፊንፊኔ የሙዚቃ ድግስ ታዋቂ ድምፃውያን በተገኙበት ይካሄዳል ተብሏል።
ኢሴት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት ኤንድ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።
የመጀመሪያው ሁነት 50 ሺህ ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቅ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ይህ ሩጫ የሰላም፣ የወንድማማችነትና የአንድነት መንፈስን ለማጠናከር “ሩጫ ለሰላምና ለወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል ተብሏል።
10 ሺህ ስኒዎችን በማዘጋጀት አዲስ ክብረወሰን የሚመዘገብበት ባህላዊ የቡና ጠጡ ሥነ-ሥርዓት፣ የኦሮሞ ባህላዊ ምግብና መጠጥ ፌስቲቫል፣ ይካሄዳል ተብሏል።
እንዲሁም የባህል አለባበስንና ሌሎች ባህላዊ እሴቶችን ያካተተ የሚስ ኢሬቻ የቁንጅና ውድድር የሚካሄድ ይሆናል።
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል አከባበር በቱሪዝሙ ዘርፍ የሀገርን ገጽታ በሚገባ የሚያሳይና የሚያስተዋውቅ ይሆናል ተብሏል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መስከረም 6/2019 ዓ.ም
