ዳሽን ባንክ እና ዓለም አቀፉ የዲጂታል ክፍያ ድርጅት ቪዛ (Visa) በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያዎችን ለማፋጠን፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት እና የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመደገፍ የሚያስችል የ5 ዓመት ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ሁለቱ ተቋማት በካርድ ክፍያዎች፣ የካርድ ስርጭትን በማስፋፋት፣ አገር አቋራጭ የክፍያ አገልግሎቶችን በማጠናከር እና ለደንበኞችና ለነጋዴዎች ዘመናዊና አስተማማኝ የክፍያ አማራጮችን በማቅረብ ላይ በትብብር እንደሚሰራ ባንኩ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡
ስምምነቱ የዳሽን ባንክን ለአገልግሎት ፈላጊዎች አስተማማኝና ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን የመስጠት አቅም የሚያጠናክር እና የአገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያፋጥን መሆኑን የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አስፋው አለሙ ገልጸዋል።
በቪዛ የምስራቅ አፍሪካና የኢትዮጵያ ካንትሪ ማናጀር ያሬድ ወልደሰንበት በበኩላቸው የቪዛን ዓለም አቀፍ ኔትወርክና የቴክኖሎጂ ልምድ ከዳሽን ባንክ የገበያ ተጽዕኖ ጋር በማጣመር በኢትዮጵያ አስተማማኝ የዲጂታል ክፍያዎችን ማስፋፋትና አዳዲስ እድሎችን መፍጠር እንደሚቻል ተናግረዋል።
መስከረም 8/2019 ዓ.ም
የዳሽን ባንክ እና ቪዛ የ5 ዓመት ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት አደረጉ
