ሊባኖስ፣ ዮርዳኖስ እና ፈረንሳይ ለሊባኖስ ጦር የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር እና የእስራኤልን ጥቃት ለማስቆም ተወያዩ

በሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን፣ በዮርዳኖሱ ንጉሥ አብደላ II እና በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መካከል በፓሪስ ውይይት ተካሂዷል።

የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፣ መሪዎቹ ለሊባኖስ ጦር እና የውስጥ ደህንነት ኃይሎች የሚደረገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ውይይቱ ለሊባኖስ ጦር እና ደህንነት ኃይሎች የሚደረገውን ድጋፍ በሚመለከተው ዓለም አቀፍ ጉባኤ መክፈቻ ዋዜማ የተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ ፈረንሳይ የሊባኖስን ጦር ለማጠናከር እና የሀገሪቱን ደህንነት የማስጠበቅ አቅምለማሳደግ ያለመውን አዲስ የአቃባ ሂደት ስብሰባ ማስተናገዷ ያለውን አስፈላጊነት ገምግመዋል።

በተጨማሪም መሪዎቹ በጋዛ፣ ዌስት ባንክ እና በምስራቅ እየሩሳሌም ባሉ ሁኔታዎች እንዲሁም በቀጣናው እየጨመረ ባለው ውጥረት ላይ ተወያይተዋል።

ሁኔታዎችን ለማረጋጋት ዓለም አቀፍ ጥረቶች እንዲጠናከሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት አውን ከፕሬዝዳንት ማክሮን ጋር በኤሊዜ ቤተ መንግሥት ባደረጉት የነጠላ ውይይት፣ በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የሚደረጉ የሰላም ድርድሮችን እና የእስራኤልን ጥቃት የማስቆም ጥረቶችን አንስተዋል።

ሀና ሰይፉ

መስከረም 8/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *