በከተማዋ የሚገኙ 1መቶ 40 ያህል የሀገር ዉስጥ አሰሪ እና ሰራተኛ አገኛኝ ኤጀንሲዎች ንግድ ፍቃዳቸዉ መሰረዙ ተገለፀ

የአዲስ አበባ ስራ እና ክህሎት ቢሮ በመዲናይቱ ከህገወጥ አስራር ጋር በተያያዘ የሀገር ዉስጥ የስራ እና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ቁጥጥር  እያደረገ ቢገኝም በህገወጥ መንገድ ተከፍተዉ የሚሰሩ ኤጀንሲዎች አሁንም መኖራቸዉን ለኢትዩ  ኤፌ ኤም ተናግሯል።

የቢሮዉ የሀገር ዉስጥ የስራ ስምሪት ፍቃድ ቁጥጥር ቡድን መሪ  አቶ በላይ ተሰማ አሁን ላይ በአዲስ አበባ 2መቶ 36 የሀገር ዉስጥ የግል ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ህጋዊ አሰራር ዉስጥ እንደሚገኙ ነግረዉናል።

በሌላ በኩል በህገወጥ መንገድ ሲሰሩ የነበሩ እና የአሰራር ክፍተት የነበረባቸዉን 1መቶ 40 ኤጀንሲዎች ተጣርተዉ ንግድ ፍቃዳቸው እንዲታገድ ቢሮዉ ማድረጉን አቶ በላይ ገልፀዋል።

ከቢሮዉ ፍቃድ ሳይወስዱ እየሰሩ ካሉ ኤጀንሲዎች ጋር አንዳንድ አሰሪዎች እየሰሩ እንደሚስተዋል የነገሩን አቶ በላይ ቢሮዉ ንግድ ፍቃዳቸው እንዲታገድ እና ከፌደራል ፖሊስ ጋር እርምጃዎች እንዲወሰድ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የስራ እና ሰራተኛን ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠት እና ከስራ ሁኔታ ጋር የተያያዘ አቤቱታ እንዲሁም ቅሬታን እየተቀበለ መሆኑን ቢሮዉ ገልፆል።

አቶ አበራ ቀጣሪ ተቋማት ሰራተኞችን ከኤጀንሲዎች በሚቀጥሩበት ወቅት አስፈላጊውን ማጣራት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 12/201 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *