የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ እና የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ በ2019 የኢሬቻ በዓል አከባበር ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ እንደገለፁት በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ መስከረም 23 ቀን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ ፣ መስከረም 24 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ ይከበራል::
በዓሉን ከዚህ ቀደሙ በላቀ መልኩ በባህላዊ አልባሳት ደምቆ እና ተውቦ ማክበር ይገባልም ብለዋል።
በአሉን ለማክበር የሚመጡ ማህበረሰቡ አባላት እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በአሉን በአንድነት በፍቅር በመከባበር እና በአንድነት እንዲያከብሩም ጥሪ አስተላልፈዋል::
በተጨማሪም የዘንድሮው የኢሬቻ በአል ከበፊቶቹ አመታት አከባበር በላቀ እና በደመቀ መልኩ ስለሚከበር ያለ ምንም የሀይማኖት ልዩነት የሁሉም እምነት ተከታይ በአንድነት እንዲያከብረው ጥሪ አስተላልፈዋል::
ሀና ሰይፉ
መስከረም 12/2019 ዓ.ም
