የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሁኑ ወቅት ዓለም በዌስት ባንክ ተጨማሪ ቀውስ አያስፈልጋትም የሚል አቋም እንዳላቸው አስታወቁ።
ሚኒስትሩ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ወቅታዊ ውጥረት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ዋሽንግተን በአካባቢው ተጨማሪ አዳዲስ የግጭት አውዶች እንዲቀሰቀሱ አትፈልግም።
ማርኮ ሩቢዮ አክለውም፣ በአሁኑ ወቅት በጋዛ፣ በሊባኖስ፣ በየመን እንዲሁም ከኢራን ጋር በተያያዘ እየታዩ ያሉ ወታደራዊ ውጥረቶችና ግጭቶች በራሳቸው እጅግ አሳሳቢ በመሆናቸው፤ ቀጠናውን ወደባሰ ቀውስ የሚያስገቡ አዳዲስ የግጭት መነሻዎች እንዳይፈጠሩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ማሳሰባቸው ተዘግቧል።
አሜሪካ በቀጠናው የሚስተዋለውን ውጥረት ለማርገብና ተጨማሪ ጦርነቶች እንዳይስፋፉ ጥረት እያደረገች መሆኑም አስረድተዋል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።
ልዑል ወልዴ
መስከረም 14/2019
