በሰሜንና በምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች የበጋው ወቅት የደረሱ ሰብሎች የሚሰበሰቡበት በመሆኑ፤በኤልኒኖ ምክንያት ሊከሰት የሚችለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ብክነት እንዳያስከትል ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
በየኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት የግብርና ሜትሮዎሎጂ ባለሙያዉ አቶ ይመራ አሰፋ እንደገለፁት፤አርሶ አደሮች ማሳቸውን በየጊዜው በመከታተል የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት እንዲሰበስቡና ወደ ጎተራ እንዲያስገቡ፣ የዘገዩ ሰብሎች ካሉ ደግሞ ዝናቡን ለምርታማነት እንዲጠቀሙበት ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።
ባለሙያዉ በመጪው የበጋ ወቅት የሚጠበቀው የአየር ጸባይ ለግብርናው ዘርፍ ሁለገብ ተፅዕኖ እንዳለው ገልጸው፤አርሶና አርብቶ አደሩ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ አሳስበዋል።
የኢንስቲትዩቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች በየክልሉ ላሉ የግብርና ቢሮዎችና ባለሙያዎች እየተላለፉ መሆኑ ተቋሙ እየገለፀ ይገኛል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መስከረም 14/2019 ዓ.ም
