ባለፉት ሰባት ዓመታት ክልሉን ሲመሩ የቆዩት አቶ ሽመልስ፤ ኃላፊነቱን በድጋሚ የተቀበሉት በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የሥራ ዘመን የመጀመሪያ ጉባዔ ላይ ነው።
በምክር ቤቱ መስራች ስብሰባ ላይ የተገኙ 509 የጨፌ አባላት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ክልሉን በፕሬዝዳንትነት መምራታቸውን እንዲቀጥሉ ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል።
በሌላ በኩል ጨፌ ኦሮሚያ አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮን አፈ ጉባዔ አድርጎ የሾመ ሲሆን፤ ወይዘሮ ዘምዘም ሻሎን ደግሞ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል።
መስከረም 18/2019 ዓ.ም
