በሴት ልጅ ግርዛት እና በጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ፈፃሚዎች ላይ  የተጣለውን የወንጀል ቅጣት የሚያሻሽል ረቂቅ ተዘጋጀ

በሴት ልጅ ግርዛት በተመለከተ የተጣለው የወንጀል ቅጣት እጅግ አነስተኛ በመሆኑ እንዲሻሻል የህግ ማሻሻያ ጥናት ለፍትህ ሚኒስትር ቀርቧል ተብሏል።

በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ጥበቃና ምላሽ መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዓለሙ ወርቁ ፤ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ በሴት ልጅ ግርዛት እና በሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ የተጣለው የወንጀል ቅጣት እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ገልፀዋል።

በዚህም እንዲሻሻል የሚያስችል ረቂቅ የህግ ማሻሻያ ሃሳብ ተዘጋጅቶ ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን ተናግረዋል ።

አቶ ዓለሙ እንደገለጹት፤ በነባሩ የወንጀል ህግ የተቀመጠው የሴት ልጅ ግርዛት ቅጣት የሦስት ወር እስራት እና የ500 ብር የገንዘብ መቀጮ ብቻ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ ቅጣት በሴቶች አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጤና ላይ ከሚደርሰው ዘርፈ ብዙ ጉዳት እና ከድርጊቱ አሰቃቂነት አንፃር እጅግ አነስተኛና በቂ የማስተማሪያ አቅም የሌለው በመሆኑ ህጉን ማሻሻል አስገዳጅ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

ጉድለት ያለባቸውን ህጎች የመለየቱ ስራ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እና የተለያዩየህግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት የተሳተፉበት መሆኑ ተጠቁሟል።

የህግ ክፍተቶቹን በጥናት የመለየት ስራው ተጠናቆ ረቂቅ ማሻሻያው ለፍትህ ሚኒስቴር የተላከ ሲሆን፣ ጉዳዩ በሚመለከተው የመንግስት አካል ታይቶ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።

ባለሙያው  ያለ ዕድሜ ጋብቻን በሚመለከት የኢትዮጵያ ህግ ከ18 ዓመት በታች የሚደረግ ጋብቻን እንደሚከለክል አስታውሰዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

መስከረም 14/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *