የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ማንኛውም ተቋም በካምፓስ፣ በመርሀ ግብር ወይም በትምህርት መስክ ከባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም ማስታወቂያ መስራትና ማሰራጨት የተከለከለ መሆኑን ተናግሯል።
ባለስልጣኑ እንደገለፀዉ በከፍተኛ እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የክትትልና ቁጥጥር መመሪያ 987/2016 መሠረት አሳሳች ማስታወቂያ የሚያሰራጭ ተቋምን እስከመዝጋት የሚያደርስ እርምጃ እንደሚያደርስ አስቀምጧል።
ተቋሙ ማስታወቂያውን ባስነገረበት መንገድ ማስተካከያ አድርጎ በአንድ ወር ውስጥ ለህዝብ ይፋ በማድረግ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርግ የሚያዘዉ መመሪያዉ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያም እንደሚሰጠዉ ገልፆል።
የተሳሳተ ማስታወቂያ ባስነገረበት ካምፓስ፣መርሀ- ግብር ወይም የትምህርት መስክ ለ2 ዓመታት የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎትእንዳይሰጥ ተቋሙ ቅጣት ይጣልበታል ተብሏል።
እነዚህን አስተዳደራዊ እርምጃዎች የተላለፈ ተቋም የተሳሳተ ማስታወቂያ ባስነገረበት ካምፓስ ወይም መርሀ-ግብር ወይም የትምህርት መስክ እንዲዘጋ ይደረጋል ሲል ባለስልጣኑ ያወጣዉ መረጃ ጠቁሟል።
ቁምነገር አየለ
መስከረም 18/2019 ዓ.ም
