የተባበሩት መንግስታት የፍልሰት ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ በሰኔ ወር በምዕራባዊ የባህር ዳርቻ ላይ ውጊያ ከተፋፋመ ወዲህ በስምንት ግዛቶች ውስጥ 1መቶ45 ሺህ3መቶ8 ሰዎች ወይም 24 ሺህ2መቶ18 ቤተሰቦች ተፈናቅለዋል።
በየመን የአይ.ኦ.ኤም ተወካይ፤ ‹‹በየሳምንቱ ሁሉንም ነገር ጥለው የሄዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሰዎችን እንቆጥራለን›› ብለዋል። ‹‹ከእነዚህ ቁጥሮች ጀርባ ልጆቻቸውን ለማዳን የሚጥሩ ወላጆች፣ ሩቅ መጓዝ የማይችሉ አረጋውያን እና ከመጀመሪያውም በጣም ጥቂት ነገር የነበራቸው ቤተሰቦች ይገኙበታል።››
አክለውም ‹‹አሁን እርዳታ ይፈልጋሉ፤ የእኛም ምላሽ እነሱ ከሚሸሹበት ፍጥነት ይልቅ ፈጣን መሆን አለበት›› ብለዋል።
አይ.ኦ.ኤም የሲቪሎችን እና የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን ጥበቃ እንዲሁም ለተፈናቀሉ ቤተሰቦች እና ለተቀባይ ማህበረሰቦች ደህንነቱ የተጠበቀና ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል።
ሁቲ በ2014 ዋና ከተማዋን ሰንዓን እና በርካታ ግዛቶችን ከተቆጣጠረ ወዲህ የመን በግጭት ውስጥ የቆየች ሲሆን፤ይህም በ2015 በሳዑዲ የሚመራው ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለውን የየመ መንግስትን ለመደገፍ ጣልቃ እንዲገባ አድርጎታል።
በያዝነዉ መስከረም ውጊያው የተፋፋመ ሲሆን፣ ሁቲዎች ስትራቴጂካዊቷን የሞካህ ከተማን ጨምሮ በአል-ሁደይዳህ እና ታኢዝ ግዛቶች ውስጥ በርካታ ቁልፍ ቦታዎችን በመቆጣጠር ወደ ባብ ኤል-ማንደብ አከባቢ መድረሳቸዉ ተዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
መስከረም 19/2019 ዓ.ም
