የሀገር ዉስጥ ኤጀንሲዎች ከሰራተኞች ደሞዝ ላይ የሚያደርጉት የግብር እና የጡረታ ተቆራጭ ገቢ ስለመደረጉ ክትትል እየተደረገ ነዉ ተባለ

በከተማዋ የሃገር ዉስጥ የስራ አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች በሰራተኞች ግብር እና የጡረታ ስም የሚቆረጡ መዋጮዎች ለሚመለከተው አካል ገቢ መደረጉን የማረጋገጥ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የከተማዋ የስራ እና ክህሎት ቢሮ ገልጿል።

ይሄን የነገሩን የአዲስ አበባ ስራ እና ክህሎት ቢሮ የሀገር ዉስጥ ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የፍቃድ ቁጥጥር ቡድን መሪዉ አቶ በላይ ተሰማ ናቸዉ።

አቶ በላይ እንደሚገልጹት፤ ኤጀንሲዎች በአግባቡ የተቆረጠዉን ገንዘብ ገቢ ማድረግ አለማድረጋቸዉ እንደ አንድ መስፈርት መቀመጡን ነግረዉናል።

ኤጀንሲዎች የሥራ ፈቃድ በሚያሳድሱበት ጊዜ ለሚመለከተው አካል ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ የቁጥጥር አሠራር ተዘርግቷል ተብሏል።

ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በሚቀጥሯቸው ሠራተኞች ስም ተቆራጭ የሚያደረጉት የግብር፣ የጡረታ መዋጮ እና ሌሎችም ለሚመለከተው አካል ገቢ መደረጋቸውን በየጊዜው ለሠራተኞች እና ለተጠቃሚ ድርጅቱ ሪፖርት የማድረግ ችግር አለባቸው በሚል ይወቀሳሉ።

በሌላ በኩል ከኤጀንሲዎቹ ተጠቃሚ ድርጅቶች ዋና ትኩረት ዝቅተኛ ዋጋ የሚያቀርብ ኤጀንሲ ማግኘት በመሆኑ ኤጀንሲዎች በዝቅተኛ ዋጋ ሠራተኞችን ያቀርባሉ በሚል ይተቻሉ።

በኢትዮጵያ ከጥራት ይልቅ ዝቅተኛ ዋጋ የቀረበበትን ሰዉ የመዉሰድ አዝማሚያ ይታይል የሚሉት አቶ በላይ፤ይህን መሠሉ የኤጀንሲዎች አሰራር የመቀነስ አዝማሚያ ቢኖረዉም ሙሉ ለሙሉ ይቀራል ማለት ግን ያዳግታል ብለዉናል።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 19/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *