ሲሚንቶዉ እንዲሸጥ የተወሰነዉ አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ነዉ፡፡
ህገ-ወጥ ደላሎችና ሌሎች የፖለቲካ አሻጥረኞች በሚሰሩት ሴራ ምክንያት የሲሚንቶና ሌሎች ምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን የንግድና እንዱስትሪ ሚንስቴር ገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎም መንግስት የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማሻሻል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፡፡
ለስራ ዕድል ፈጠራ ሚናው ከፍተኛ ለሆነው የግንባታው ዘርፍ በዋና ግብዓትነት የሚያገለግለውን የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት ስርዓትና የዋጋ መጨመር ለማስተካከል በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች አማካኝነት የቀረበ 50ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከ376 ብር በታች እንዲሸጥ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች አማካኝነት የቀረበ 50ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከ377 ብር በታች
ደርባ 343.35
ሙገር 352.63
ሐበሻ 364.39 እና 376.28
እንዲሸጥ መወሰኑን ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም የስርጭት ፍትሀዊነቱን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለህብረተሰቡ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ መወሰኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም
