ሰሜን ኮሪያዊያን በኪም ጆንግ-ኡን ክብደት መቀነስ መጨነቃቸው ተሰምቷል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ድንገተኛ የሆነ ክብደት መቀነስ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መታየቱ ተሰምቷል ፡፡

የኪም የጤና ሁኔታን በተመለከተ በሃገሪቱ መንግስት ሚዲያዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ማውራት በአብዛኛውን ጊዜ የተከለከለ ነው ፡፡

ይሁንና የአገሪቱ ዋና የቴሌቪዥን ጣቢያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኪምን ቀጫጭን የሚመስሉ የሰውነት ክፍሎችን የሚያሳዩ ቀረፃዎችን አሳይቷል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ በሥልጣን በቆዩባቸው አሥርት ዓመታት ውስጥ ስለ ጤንነት ሁኔታቸው የማያቋርጡ ወሬዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ቢኖሩም ስለ ኪም በሃገሪቱ መንግሥት ዕውቅና የተሰጠው ትክክለኛ መረጃም የለም ፡፡

በአገሪቱ ዋና የቴሌቪዥን ጣቢያ በሆነው ኮሪያ ሴንትራል ቴሌቪዥን ላይ የታዩት ሁለት የቅርብ ጊዜያት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ግን የኪም ጤንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ማመላከቱ ተነግሯል ፡፡

እ.ኤ.አ. በ 2014 ኪም ጆንግ-ኡን ለ 40 ቀናት ጠፍተው ዳግመኛ ሲወጡ ከዘራ ይዘው የታዩ ሲሆን ቁርጭምጭሚታቸው ላይ ቀዶ ጥገና ማድረጋቸው ነው የተነገረው ፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ዕድሜ 37 ዓመት እንደሆነ የተነገረም ሲሆን ፣ ኪም ከባድ የትንባሆ እና የመጠጥ ሱስ እንዳለባቸው ቢቢሲ በዘገባው አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *