አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ላብራቶሪ እንዳመለጠ የምትናገረው ግምት ነው ሲል የአለም ጤና ድርጅት አጣጣለ።

አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ላብራቶሪ እንዳመለጠ የምትናገረው ግምት ነው ሲል የአለም ጤና ድርጅት አጣጣለ።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ ቫይረሱ ከቻይና ላብራቶሪ አምልጦ እንደወጣ መረጃ አለን እያሉ ነው፤ ካላቸው ወዲህ ይቡሉ ብሏል የአለም ጤና ድርጅት፡፡

መንግስታዊ ሀላፊዎች ሳይንሳዊ መረጃን መሰረት አድርገው እንዲናገሩም ጥሪውን አቅርቧል ተቋሙ፡፡

ፖምፒዮ ከቻይና ከተማ ዉሀን ከሚገኝ ላብራቶሪ አምልጦ እንደወጣ በቂ ማስረጃ አለን ቢሉም ሰው ሰራሽ ቫይረስ ነው የሚል ነገር አልተናገሩም፡፡

የአለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎች ኤክስፐርት ዶ/ር ማይክ ርያን ከጀኔቫ ሆነው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ስለ ቫይረሱ መነሻ የሚያሳይ ከአሜሪካ የደረሰን ምንም ማስረጃ የለም ብለዋል፡፡

እንደኛ እስካሁን አሜሪካ የምትለው ሁሉ ግምት ነው ብለዋል፡፡

ስለ ቫይረሱ መነሻ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነውና ማንኛውንም ማስረጃ ለመቀበል የአለም ጤና ድርጅት ፍልጎትም ዝግጁነትም አለው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ካላችሁ ማስረጃውን በመስጠት ወረርሽኙን ለመግታት የምናደርገውን ጥረት አግዙ እንጂ ትንበያ አይጠቅምም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *