በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቱ ካለፈ ሰው የኤቲኤም ካርድ በመስረቅ ገንዘብ ያወጣችው ነርስ በእስር ተቀጣች፡፡

በአሜሪካ ስታተን አይስላንድ ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ ሂወቱ ያለፈን ሰው ክሬዲት ካርድ የሰረቀችው ነርስ በእስራት እንደተቀጣች ኒዮርክ ፖስት ዘግቧል፡፡

የ43 አመቷ ዳንኤሊ ኮንቲ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሂወታቸው ያለፈውን የ70 አመት አዛውንት ክሬዲት ካርድ በመስረቅ አንድ መቶ የአሜሪካ ዶላር ከአካውንቱ እንደወሰደች ተረጋግጣል ነው የተባለው፡፡

የሆስፒታሉ ቃል አቃባይ ኮንቲ በአይስላንድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል 2007 ጀምሮ እስካሁን በሆስፒታሉ በመስራት ላይ ትገኛለችም ተብሏል፡፡

ባሁኑ ሰአት ዳንኤሊ ኮንቲ ለጊዜው በሆስፒታሉ ቅጣት የተጣለባት ሲሆን የፍርድቤት ውሳኔ ከታየ በኃላም ከስራ ልተሰናበት እንደምትችል ነው የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ የገለጹት፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሆስፒታሉ ከፖሊስ ጋር በጋራ በመሆንም የራሱን ተጨማሪ ምርመራ ያደርጋልም ነው የተባለው፡፡

የሟች ሴት ልጅ ከአባቷ አካውንት ላይ አንድ መቶ የአሜሪካን ዶላር እንደተሰረቀ ለፖሊስ ካሳወቀች በኃላ ነው ተጠርጣሪዋ ነርስ በቁጥጥር የዋለችው፡፡

የግለሰቧን ጉዳዩን እየተከታተለ የሚገኘው ፖሊስ እንደተናገረው በተለያዩ ጊዜያቶች እጅግ የሚገርሙ ስርቆቶች ይፈጸማሉ ይሄኛው ስርቆት ግን እጅግ አስነዋሪ እና ለመገመትም የሚያስቸግር ሲል ነው የተናገረው፡፡

ህይወት የሚያድኑ የህክምና ባለሙያዎች እንዳሉ ሁሉ ህይወት ካለፈም በኃላ የሚሰርቁ ባለሙያዎች እንዳሉ ግን መረሳት የለበትም ሲሉም መናገራቸውን ዘገባው በዘገባው ተጠቅሷል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *