ናይጄሪያ የንግድ አንቅስቃሴዎች አንዲቆሙ ያወጣሁትን ህግ ተላልፈዋል ያለቻቸውን ሁለት ሆቴሎች አፈረሰች፡፡

በዘይት ሀብት በበለፀገችው የናይጄሪያ ደቡባዊ ክልል የሚገኙ ሁለት ሆቴሎች መንግስት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሰው በመገኘታቸው እንዲፈርሱ መደረጉን የአካባቢው ባስልጣናት ተናግረዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በሚል የሀገሪቱ መንግሰት የጣለውን የእንቅሰቃሴ ገደብ ተከትሎ ሆቴሎች እንዲዘጉ ተደጋጋሚ መልዕክት ቢተላለፈም የሆቴሉ ባቤቶች ግን አሻፈረኝ ብለው ነበር ተብሏል፡፡

መንግስት ይህን እገዳ ሲጥል በክልሉ በሚገኙ ሆቴሎች ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ መሆኑን ባስልጣናቱ ጠቅሰዋል፡፡

እንዲፈርሱ በተደረገው ሆቴል ውስጥ ግን የኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው ስለመገኘቱ ያሉት ነገር የለም፡፡

የሁለቱም ሆቴል ስራ አስኪያጆች የታሰሩ ሲሆን የሆቴሉ ባለቤቶች ግን ሆቴላቸው ስለመከፈቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሀገሪቱ 4ሺ 641 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 150 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

901 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *