ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት 20 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት፣ የ2012 ዓ.ም ክረምት #አረንጓዴዐሻራ የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር መወያየታቸው ተገልጿል፡፡

በውይይቱ የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው አባላት፣ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት፣ የክልል ፕሬዚደንቶች፣ ሕዝቡን የማነሳሳት ሥራን የሚከውኑ ተጽዕኖ አሳዳሪ ግለሰቦችን ጨምሮ ዐበይት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡

ባለፈው የችግኝ ተከላ ወቅት ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ ተነሣሥተዋል፣ ንቃት የተሞላ የመንግሥት አመራር ታይቷል፣ የተቋማት ትብብር እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተስተውሏል፡፡

እነዚህን መልካም ተሞክሮዎች ማስፋት እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነሥቷል፡፡ የዚህ ዓመት ግብ 5 ቢሊየን ችግኞችን መትከል ሲሆን፣ ለዚህ የሚያበቃ ብዛት ያለው ችግኘ እንዲፈላ ቅድመ ዝግጅት ሲካሄድ መቆየቱ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጅማሮዎችን የማስቀጠልን ጠቃሚነት አንሥተው፣ #አረንጓዴዐሻራ በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊየን ችግኞችን በመትከል እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም፣ አዲስ አበባን የማስዋብ፣ የከተማ ቱሪዝምን የማስፋፋትና ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማን መፍጠር ዓላማው የሆነው ፕሮጀክት ያካተታቸውን የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ገልጸዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ነው
ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *