ከአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በባለፈው ዓመት በተፈጠረ ግጭት ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ 853 ዜጎች ወደ ቀያቸው ተመለሱ::

አማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ሁከት ምክንያት በጓንጓ ወረዳ ራንች መጠለያ ካምፕ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ነበሩበት ወደ ማንዱራ ወረዳ ተመልሰዋል።

ወረዳው ተፈናቃዮች ወደ ነበሩበት ሲመለሱ መደበኛ የእርሻ ስራዎችን እንዲያከናውኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክክል ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት በማስመለሱ ሂደት የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች በትኩረት እየሰሩም ይገኛሉ።

በቀጠናው ሰላምን በማስፈን በሁለቱም ክልሎች በኩል ከቀያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ነበሩበት ለማስመለስ በመከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ይታወቃል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *