የቻይና ምርት የሆነ 10 ሚሊየን የፊት መሸፈኛ ጭምብል በአውሮፓ ገበያ እንዳይቀርብ ታገደ።

አውሮፓ በቻይና የተመረተ ጥራት የጎደለው 10 ሚሊየን የፌት መሸፈኛ ጭብል ለተጠቃሚዎች እንዳይሰራጭ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ማገዱን አስታውቋል ።

አልጄዚራ እንደዘገበው ፣ እንግሊዝን ጨምሮ ሁለት የህብረቱ አባል ሀገራት ከቻይና የገባው የፌት መሸፈኛ ጭብል ከደረጃ በታች በመሆኑ ቅሬታ ለህብረቱ አቅርበዋል ተብሏል ።

ቻይና 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ጭብል ለአዉሮፓ ሀገራት ያቀረበች ቢሆንም ለተጠቃሚዎች ለማሰራጨት በህክምና ባለሙያዎች የተቀመጠውን እና የአውሮፓ ደረጃን አለሟሟላቱን ተናግረዋል ።

የኔዘርላንድ መንግስትም በተመሳሳይ ጥራት የጎደለው ጭብል ከቻይና እንደመጣለት ቅሬታ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል።

የአውሮፓ ህብረት ኮምሽን የእርምጃውን አይነት ባይገልጽም አስፈላጊ ከሆነ ቻይና ላይ እርምጃዎች ይወሰዳል ብሏል ።

በአውሮፓ ህብረት ፈንድ ከቻይና መንግስት በግዥ የተከማቸ የፌት መሸፈኛ ጭብል በ6 ሳንምት ውስጥ ለተጠቃሚዎች ለማሰራጨት እቅድ ተይዞ ነበር ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *