ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ በዓለማችን 106 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ እንዳለው በዓለማችን በየቀኑ የአዳዲስ ተጠቂ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 106 ሺህ ሰዎች በቫረሱ መያዛቸውን ሪፖርት መደረጉን አስታውቆ ይህ አሃዝ ደግሞ ከእስካሁኑ የእለት ሪፖርት ከፍተኛው ነው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደተናገሩት በአንድ ቀን ከተመዘገበው የተጠቂዎች ቁጥር ውስጥ 75 በመቶዎቹ በአራት ሀገራት የሚገኙ ናቸው ብለዋል።

ዓለም አሁንም ከዚህ ወረሽኝ ጋር ረጅም ርቀት ትጓዛለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ይህ ቢሆንም ፣ አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የጥብቅ ገደቦችን ማንሳት ጀምረዋል ፡፡
አሜሪካ ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተጠቂዎች ሲኖራት ከ92 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በሞት ሀገሪቱ ከመላው አለም የከፋ አደጋ የደረሰባት ሆናለች፡፡

በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃው ሰው አምስት ሚሊየን ደርሷል፡፡

ሆኖም በርካታ ጉዳዮች ሳይታወቁ ወይም ሳይመረመሩ ሊቀሩ እንደሚችሉ እና ትክክለኛው የተጠቂዎች ቁጥር ከዚህም በጣም ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል የጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ መረጃ ይጠቁማል።

በቫይረሱ በእጅጎ ከተጎዱት ሀገራት መካከልም በአሜሪካ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሲጠቁ በሩሲያ 308 ሺህ 705 ሰዎች ፣ብራዚል 291 ሺህ 579 ፣ እንግሊዝ 249 ሺህ 619 ሰዎች እንዲሁም በስፔን ደግሞ 232 ሺህ 555 ሰዎች ሲጠቁ የሟቾች ቁጥር በአለም ዙሪያ 328 ሺህ 79 ደርሷል፡፡

በአፍሪካ ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ እና ሞሮኮ በተጠቂዎች ቁጥር ሲመሩ ግብጽ ደግሞ በሟቾች ቁጥር አህጉሪቱን ይመራሉ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *