የኦስትሪያው ፕሬዝዳንት በአገራቸው የተጣለዉን የሰዓት እላፊ ገደብ ተላልፈዉ በመገኘታቸዉ ይቅርታ ጠየቁ፡፡

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል በሀገሪቱ ዋና ከተማ ቬይና ካፌዎችና ሬስቶራንቶች ተዘግተዉ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ስራዎቻቸዉን የሚያከናዉኑባቸዉ ሰዓታት ተገድቦ ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

በተለይም የቁርስና ምሳ ሰዓት አካባቢ ስራዎቻቸዉን ሰርተዉ ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ዝግ እንዲያደርጉ ይጠቁማል፡፡

የ76 ዓመቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቫን ዲር ቤሌን ግን ከባለቤታቸዉና ከ2 ጓደኞቻቸዉ ጋር በመሆን ከተቀመጠዉ የሰዓት ገደብ በላይ በአንድ ሬስቶራንት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አምሽተዉ ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱም የሰራሁት ስህተት ነዉ፣ለበርካታ ቀናት ቤቴ ነበር ያሳለፍኩት፤ከጓደኞቼ ጋር ስናወራ ሰዓቱ በዛ ልክ መምሸቱን አላስተዋልኩም ነበር ለዚህም በትዊተር ገጻቸው ላይ ይቅርታ መጠየቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኦስትሪያ ቀደም ሲል የተጣሉ ጠንካራ ማዕቀቦችን በማላላት በካፌና ሬስቶራንቶች እስከ 10 ሰዎች መሰባሰብ እንደሚችሉና፣ሱቆችና መናፈሻ ቦታዎች ክፍት እንዲሆኑ ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ወስናለች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.