የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች አካላዊ ንክኪን የሚፈቅድ ልምምድ ለመጀመር ተስማሙ::

 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ‹‹ Project Restart ››/ ፕሪምየር ሊጉን ከቆመት ለማስጀመር የተያዘው ውጥን አካል የሆነው ሁለተኛ ምዕራፍ አካል የሆነውን አካላዊ ንክኪ የሚፈቅድ ልምምድ ለመጀመር በሙሉ ድምጽ ወስነዋል፡፡ ውሳኔው ተጫዋቾች ‹‹በቡድን ልምድ መስራት እና ሸርቴዎችንም እንዲወርዱ ይፈቀድላቸዋል፡፡ በተቻለ መጠን ግን አላስፈላጊ ንክኪዎችን እንዲያስወግዱም ይጠየቃሉ›› ይላል ፕሪምየር ሊጉ ያወጣው መግለጫ፡፡

‹‹ሁኔታዎች ሲፈቅዱ›› የውድድር ዘመኑን ለመጀመር ውይይቶች መደረጋቸውን እንደሚቀጥሉም ጨምሮ አስፍሯል፡፡ የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ተጫዋቾች እና የቡድኑ ሌሎች አባላት በሳምንት ሁለት ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉም ተገልጿል፡፡ እስካሁን በፕሪምየር ሊጉ ምርመራ ከተደረገላቸው 1744 ተጫዋቾች እና የቡድን አባላት ስምንቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ የሶስተኛ ዙር ምርመራ ውጤት ዛሬ ማምሻውን ይፋ እንደሚደረግም ተነግሯል፡፡

አካላዊ ንክኪ የሚፈቅደውን ልምምድ ለመጀመር ውሳኔ ላይ የተደረሰው ከክለቦች፣ተጫዋቾች፣አሰልጣኞች ፣ፕሮፌሽናል እግርኳስ ማህበር (PFA)፣ የሊግ አሰልጣኞች ማህበር (LMA) እና መንግስት የተሳተፉበት ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው፡፡ የ‹‹ፕሮጀክት ሪስታርት›› ሶስተኛው ምዕራፍ ወደተለመደው የልምምድ መርሃግብር እና የነጥብ ጨዋታዎች የሚያደርስ ዕቅድ ይዟል፡፡ ባለፈው አርብ የፕሪምየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሪቻርድ ማስተርስ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የውድድር ዘመኑ በመጪው ሰኔ እንደሚጀመር ‹‹ከመቼውም ጊዜ በላይ እርግጠኞች ነን›› ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ፕሪምየር ሊጉ ለመጠናቀቅ ቀሪዎቹን 92 ጨዋታዎችን ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡

 የፕሪምየር ሊጉ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ከንክኪ ውጪ የሆነ ልምምድ መጀመራቸው ይታወቃል፡፡ ክለቦቹ ነገ ገለልተኛ ስታዲየሞችን መጠቀምን ፣ አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮ ፕሪምየር ሊጉ እዚሁ ላይ እንዲጠናቀቅ ቢገደድ እንዴት ባለ መልኩ መቋጨት እንደሚኖርበት እና የቴሌቪዥን ስርጭት መብት ለገዙ ተቋማት ገንዘብ ተመላሽ በሚያደርጉበት መንገድ ድምጽ ይሰጣሉ ፡፡ በሌሎች ጉዳዮች ላይም ይወያያሉ ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *