በአሜሪካ ያለው የዘር መድሎ በአፋጣኝ እነዲቆም የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉትይሬዝ ተናገሩ፡፡

አንቶኒዮ ጉትይሬዝ አሜሪካዊያን በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞአቸውን እንዲያሰሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉትይሬዝ ከሰሞኑ በሀገሪቱ የተከሰተውን ድርጊት አውግዘው ድርጊቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ግጭት እንዲቆም ጥሪቸውን አቅርበዋል፡፡

ዜጎች ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ አለባቸው የሀገሪቱ መንግስት የሚያሳልፈውን ውሳኔም መጠበቅና ማክበር አለባቸው ሲሉም ነው ዋና ጸሀፊው የተናገሩት፡፡

የጸጥታ ሀይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየወሰዱት ያለውን ከመጠን በላይ የሆነ ሀይል እንዲያቆሙም መልእክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ የማቅረብ መብታቻው ሊከበርላቸው ይገባል የመንግስት ባለስልጣናትም ጥያቄያቸውን መመለስ አለባቸው ብለዋል፡፡

አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት በተለየ ብዙሀነት የሚታይባት ሀገር ነች ብዙሀነት ደግሞ ስጋት ሊሆን አይገባም ነው ያሉት፡፡

ብዙሀነት ውጤታማ ሊሆን የሚችለው አንድነት እና መተባበር ሲኖር ነው አንድነት ደግሞ ትልቋን አሜሪካ ይበልጥኑ ያሳድጋታል ብለዋል፡፡

በአሜሪካ በተደጋጋሚ እየተስተዋለ ያለው ዘር ተኮር ጥቃት ባፋጣኝ መቆም ካልቻለ ሀገሪቷን ትልቅ ዋጋ ያስከፍላታል ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *