በጅቡቲ የአየር ሀይል አብራሪ ላይ የደረሰውን ድብደባ ተከትሉ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።

በጅቡቲ አየር ሃይል ውስጥ የሚሰራ አነድ የጦር ጀት አብራሪ በአገሩ ያለውን አገዛዝ ተቃውሞ ኮብልሎ ነበር።

ይህ ኮብላይ የጦር ጀት አብራሪ ወደ ኢትዮጵያ እንደኮበለለ ቢነገርም የኢትዮጵያ መነገስት ከጅቡቲ መንግስት ጋር ባለው ስምምነት መሰረት ተላልፎ መሰጠቱ ተገልጿል።

የጅቡቲ መንግስትም ይህ የጦር ጀት አብራሪ በእጁ ከገባ በኋላ ድብደባ እንደተፈጸመበት ዘገባዎእ በመውጣት ላይ ናቸው።

በቁጥጥር ስር የዋለው የአየር ኃይል አብራሪ ድብደባ እንደተፈጸመበት የሚያመለክቱ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሉም በጅቡቲ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።

ቢቢሲ እንዳወራው በሀገሪቱ ያሉ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ ባይሆኑም ፉአድ ዩሱፍ አሊ በሚያዝያ ወር ኢትዮጵያ ውስጥ ተይዞ ወደ ጅቡቲ ተላልፉ እንደተሰጠ ይታመናል፡፡

በድብቅ በተቀረጸ ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው ፖይለቱ የደረሰበት ድብደባ ለህይወቱ እንዲሚያሰጋው ያሳያል፡፡

ጠበቃው ባለፈው ወር አሊ በጎበኙበት ወቅት ከፍተኛ ማሰቃየት እንደተፈጸመበት የሚያሳዩ ምልክቶች ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን በታገተው ፖይለት ዙሪያ ዘገባ የሚሰሩ ሁለት ጋዜጠኞቹ ከአርብ እለት ጀምረው በጅቡቲ እንደታሰሩበት አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.