በአንድ ጀምበር ሚለየነር የሆነው ታንዛናዊ ባህላዊ ማዕድን ቁፋሪ፡፡

በበባህላዊ መንገድ ማዕድን ይቆፍር የነበረው ታንዛናዊ ባገኛቸው ሁለት ታንዛናይት የተባሉ ማዕድናት ነው ከሀብት ማማ ላይ በአንዴ የወጣው፡፡

ይህ ስሙ ሳኒኑ ላይዘር የተባለው ግለሰብ በአንድ ላይ 15 ኪሎ ግራም የሚመዝኑትን ሁለት ግዙፍ ታንዛናይት ማዕድን 3.4 ሚሊየን ዶላር እንደሸጣቸው የሀገሪቱ የማዕድን ሚኒስትር ማስታወቁን ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡

ከ30 በላይ ልጆች እንዳሉት የሚነገረው ይህ ማዕድን ቁፋሪ ያገኘው የከበረ ማዕድን በሀገሪቱ ታሪክ ከ15 አመታት ወዲህ የመጀመሪያው ነው፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ጆን ማጎፋሊ ለግለሰቡ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህ አይነት የከበረ ማዕድን በሰሜን ታንዛኒያ ብቻ የሚገኝ ሲሆን ጌጣጌጦችን ለመሥራት የሚያገለግል ነው ፡፡

ማዕድኑ በምድር ላይ ካሉ በጣም የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው ፣ እናም አንድ የአከባቢ ጂኦሎጂስት እንደሚለው ይህ ማዕድን በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ተሟጦ ሊያልቅ ይችላል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *