በህጻናት ጥቃት ዙርያ የህግ ማሻሻያ እንዲደረግ የፊርማ ማሰባሰብ ስራ ተጀመረ፡፡

በህጻናት ላይ እየደረሰ ያለው ጾታዊ ጥቃት ተደባብሶ መቅረት የለበትም በዚህም የህግ ማሻሻያም መደረግ አለበት ነው የተባለው፡፡

ይህንንም ተከትሎ የህግ ማሻሻያ እንዲደረግ የሚጠይቅ የኦላይን ፊርማ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራም ነው የሚገኝው፡፡

እስካሁን ድረስ ከህብረተሰቡ ከ20 ሺህ በላይ ፊርማዎች ማሰባሰብም ተችሏል።

ከህዝቡ የተሰበሰበው ፊርማ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰላም ሚኒስትር እና ለሌሎች ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት የሚቀርብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

“ዝም አልልም” ማህበረሳባዊ እንቅስቃሴ በህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጾታዊ ጥቃት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይጋበል በዚህም መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት የህግ ማሻሻያ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

እንቅስቃሴውን እያደረጉ የሚገኙት እነዚህ ግለሰቦች በህጻናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ድምጽ ሆኖ የሚመለከታቸው የመንግስትና መንግስታዊ የልሆኑ አካላት ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አለባቸው ብለዋል፡፡

ዝም አልልም እንቅስቃሴ የህጻናት ደህንነት ጉዳይ የሚመለከታቸው ተቋማትን የማንቃት የማገዝ እና በህብረተሰቡ እና በተቋማቱ ድልድይ የመሆንን ተግባር ያደረገ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ይህንን እንቅስቃሴ በዋናነት የጀመረችው አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ የህጻናት የመደፈርን ጉዳይ ሀገር አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ እና ሁሉም አካላት በያሉበት የየራሳቸውና የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ የመቀስቀስ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግራለች፡፡

እንቅስቃሴው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶም የተዘናጉትን በማንቃት እና በቸልተኝነት ውስጥ የተዋጡት ላይ ደግሞ ጫና በማሳደር ሁሉም ወገን የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲጀምር የማንቃት ስራ ስርተናል ብላለች፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *