ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3693 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5846 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 52 ናሙናዎች (28 ከጤና ተቋም እና 24 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 4 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ባለፈ አንድ በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበረ ሰው ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 103 ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 298 ሰዎች (200 ከአዲስ አበባ፣ 87 ከሶማሊ ክልል፣ 9 ከአማራ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2430 ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *