የስፔን የቀድሞው ንጉሥ ጃዋን ካርሎስ አገር ለቀው ተሰደዱ።

እንደ ሀገሪቱ ንጉሳዊ ቤተመንግስት መረጃ የስፔን የቀድሞ ንጉስ ጁዋን ካርሎስ ሀገሪቱን ለቀው እስከመውጣት የሚደርስ ውሳኔ ያስወሰናቸው ከሳምንታት በፊት ከሙስና ጋር ተያይዞ መከሰሳቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የ82 ዓመቱ የቀድሞው ንጉስ ከ6ዓመት በፊት ንግስናቸውን ላስተላለፉለት ልጃቸው ፊሊፕ ሀገሪቱን ለመልቀቅ መወሰናቸውን በይፋዊ ደብዳቤ ፅፈው መላካቸውንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡

አቃቤ ህግ ክሱን በተመለከተ ሊያነጋግረኝ ከፈለገ በማንኛውም ሰዓት አለሁ ሲሉ በደብዳቤአቸው ላይ ማስፈራቸውም ተነገሯል፡፡

ባለፈው ወር ነበር የስፔን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የፍጥነት ባቡር ግንባታ ኮንትራት ውስጥ የቀድሞ ንጉስን ተሳትፎ በተመለከተ የምርመራን መዝገብ የከፈተው፡፡

የቀድሞው ንጉሠ አሁን የት እንደሚገኙ የተገለጸ ነገር የለም ፣ ነገር ግን የስፔን መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ከሆነ የቀድሞው ንጉስ በሀገሪቱ ውስጥ የሉም፡፡

በ አውሮፓውያኑ 1975 ከጄኔራል ፍራንኮ ሞት በኋላ ስፔንን ከአምባገነናዊ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመለወጥ ህዝቡን በብቃት የመሩት ታሪካዊው መሪ ላይ ይህ የሙስና ክስ መመስረቱ ታሪካቸውን እንደሚያጠለሸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በትግስት ዘላለም
ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *