የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሊባኖስ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡

የተባበሩት መንገግስታ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የተከሰተውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ ነው ሀገሪቱን በማንኛውም መልኩ ለመደገፍ ዝግጁ ነን ሲሉ የተደመጡት፡፡

ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ እያሳደረ ከሚገኘው ተፅዕኖ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመላቀቅ እየታገለች ባለችበት በዚህ ወቅት ከፍተኛ ፍንዳታ መድረሱ ሀገሪቱን እጅግ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ከቷታል ሲሉም ዋና ፀሀፊው ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ተጠቂ ለሆኑ ከ150 በላይ የቤተሰብ አባላትም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጉተሬዝ አስከፊውን አደጋ ተከትሎ ድጋፍ ለሚሹ ሊባኖሳውያን በሙሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በአደጋው ለተጎዱ እና በእሳቱ ለቆሰሉ ወገኖች ማከሚያነት የሚውል 20 ቶን የሚመዝን የህክምና ቁሳቁሶች ከዓለም ጤና ድርጅት መበርከቱንና የህክምና ቁሳቁአሶቹም ቤይሩት መድረሳቸውን ጉተሬዝ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አደጋው በደረሰ በሰዓታት ውስጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወኪል እና በሊባኖስ የሰብአዊ መብት አስተባባሪ ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚውል የ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ ድጋፍ መደረጉንም ዋና ጸሀፊው ተናግረዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ አስተባባሪዎች እንዲሁም የ6 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን አክለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሊባኖስን የሚገኘውን ቀይ መስቀል ና ሌሎችንም ተቋማት እየደገፈ ይገኛል ማለታቸውንም ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *