በማሊ ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረው ወታደራዊ ሀይል የሶስት ዓመት የሽግግር መንግስት ለማቋቋም እንደሚፈልግ ይፋ አደረገ፡፡

ይህ የሽግግር መንግስት በአንድ ወታደራዊ አካል የሚመራ ሲሆን ምናልባትም የቀድሞው የማሊ ጦር መሪ ጀነራል ማሀማኔ ቱሬ የሽግግር መንግስቱ መሪ ሊሆኑ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ጉድላክ ዮናታን ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ወደ ማሊ ያቀኑ ሲሆን ከወታደራዊ ጁንታው ጋር መምከራቸው ታውቋል፡፡

በንግግራቸውም ወታደራዊ ሀይሉ ስልጣን ለሲቪል እንዲያስረክብና የሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም መጠየቃቸውን የስፑትኒክ ዘገባ አትቷል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በመፈንቅለ መንግስት የተባረሩት ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ቦባካር ኬይታ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉን ምንጮች ገልፀዋል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *