የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ውስጥ በ900 ወረዳዎች መከሰቱን የፌደራል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ በሁሉም ክልሎች እና ዞኖች የተዛመተ ሲሆን በ900 ያህል ወረዳዎችም ቫይረሱ እንደተሰራጨ ነው የተገለጸው፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ለአንድ ሚሊየን 78 ሺህ ሰዎች የኮሮና ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 60 ሺህ 784 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

አሁን ላይ 22 ሺህ 677 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን 307 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡

949 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን እንዳጡ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰአት በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስን በመመርመር ላይ የሚገኙ 53 ላብራቶሪዎች ሰኖሩ 12ቱ በአዲስ አበባ ሲገኙ 41 ላብራቶሪዎች በክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም በአሁኑ ሰአት 9 ተጨማሪ ላብራቶሪዎች የምርመራ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ኢንስቲትዩቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቅል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጷግሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *