አሜሪካ በቀድሞ የጋምቢያ ፕሬዘዳንት ቀዳማዊት እመቤት ዜነብ ጃሜህ ላይ ማዕቀብ ጣለች፡፡

በጋምቢያው ፕሬዘዳንት የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ዜነብ ጃሜህ በባለቤታቸው በፕሬዘዳንት ያህያ ጃሜህ የሥልጣን ዘመን በሰሩት ሙስና ከተከሰሱ በኋላ አሜሪካም ማዕቀብ መጣሏን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ረገድ ተሳታፊ እንደነበሩ ተጠርጣሪ የነበሩ ሲሆን በውጭ ሀገር ያፈሯቸው ንብረቶች እንዳይንቀሳቀሱ ማዕቀብ መጣሉን የአሜሪካ ግምጃ ቤት አስታውቋል፡፡

ጃሜህ እንደ አውሮፓውያኑ በ 2017 ከስልጣን ከመባረራቸው በፊት 50 ሚሊዮን ዶላር ያህል መስረቃቸውን የጋምቢያ ፍትህ ሚኒስቴር ገልጧል፡፡

ጥንዶቹ ከዚህ በፊት በግላቸው ምንም ዓይነት ጥፋት አለመፈፀማቸውን ክደዋል ፡፡

በሔኖክ አስራት
መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *