ብሔራዊ የፖሊስ ዶክትሪን ይፋ ተደረገ።

በሰላም ሚንስቴር የተዘጋጀው ይህ የፖሊስ ዶክትሩን ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ተደርጓል።

ሰነዱ ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ገለልተኛ ፖሊስ ለመገንባት የተጀመረው ስራ ውጤት ነው ተብሏል።

የሰላም ሚ/ር ሙፈርያት ካሚል ‘ህዝብ አክባሪና ዘመን ተሻጋሪ ፖሊስ እንገነባለን’ በሚል መሪ ቃል ፤ የፖሊስ ተቋማችን የሚጠበቅበትንና የሚመራበትን የፖሊስ ዶክትሪን ይፋ ማድረጊያ ስነስርአትን አስጀምረዋል።

በዚህ ወቅት ሚንስትሯ እንደተናገሩት ዛሬ ይፋ የምናደርግላችሁ ዶክትሪን ፤ ስርአትን ሳይሆን ህዝብን የሚያገለግል፣ ስርአት በተቀየረ ቁጥር ከዜሮ የማይጀምር፣ ወታደራዊ ያልሆነ፣ያልተማከለ፣ ዜግች በፖለቲካ አመለካከታቸው የፖሊስን ፍትሀዊ አገልግሎት የማያጡበት የፖሊስን ተቋም መጀመር ማብሰርያ ነው ብለዋል።

በአሁን ሰአት ዶክትሪኑ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *