የእንጦጦ ፓርክ ነገ ይመረቃል ተባለ።

የጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የእንጦጦ ፓርክ ነገ ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

ፓርኩ አገርኛ ስያሜዎችን እና መዝናኛ ዘርፎችን ባካተተ መንገድ የተገነባ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተገልጿል።

የፓርኩ ምርቃት ከተከናወነ በኋላም ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

በሳሙኤል አባተ
መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *