ከ14 በላይ የነዳጅ ማደያ ያላት ሐዋሳ ከተማ በነዳጅ ጥቁር ገበያ እየታመሰች ነው።

በከተማዋ አንድ ሊትር ቤንዚን እስከ 50 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።

ከተለያዩ ነዳጅ ማደያዎች በሌሊት በበርሜል እና ጀሪካን ቤንዚን በየመንደሩ እየተሸጠ በመሆኑ ከማዳያ ነዳጅ ለመቅዳት ለሰታት ሰልፍ ለመሰለፍ መገደዳቸውን አሽከርካሪዎች ለኢትዬ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከየመንደሩ እና ነዳጅ ማደያ አካባቢ ቤንዚን የመግዛትና የመጠቀም ሁኔታው በመኖሩ የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች መንግስት ባስቀመጠው የነዳጅ ዋጋ ተመን ለመግዛት ከአቅም በላይ እንደሆባቸውም ነግረውናል።

ጠዋትም መጣን ያው ነወ ከሰዓት ይቀንሳል ብለን መጣን ያው ነው፣ ሶስት አራት ነዳጅ ማደያ ላይ ነዳጅ መኖሩን አረጋግጠናል የሚሉት እነዚህ ሾፌሮች
መንግስት ህግ እንዲያስከብር ጠይቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የአዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ለታሞን በጉዳዩ ዙሪያ ጠይቋል።

በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦት እና ማጓጓዝ ላይ ችግሮች ቢኖሩም በሕገ ወጥ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች የሚወጣውን ነዳጅ መልሰው ለጥቁር ገበያ ሚያቀርቡት እራሳቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሾፌሬች ናቸው ብለዋል።

ሀላፊው የአጠቃቀም ችግርም መኖሩን ገልጸው ከ 6 በላይ የከተማዋ አዋሳኝ ወረዳዎች ነዳጅ ማደያ ባለመኖሩ ለጥቁር ገበያ መስፋፋት ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በአዋሳ ከተማ የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭት ላይ አዲስ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት ከፖሊስ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ግብረ ሐይል በማቋቋም ሕገወጦች ላይ አስተማሪ ዕርምጃዎች ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑን አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *