ከ90 በላይ ዜጎቿ በዝሆኖች የተገደሉባት ኬንያ ጉዳዩ እንዳሳሰባት አስታወቀች።

የሀገሪቱ የዱር እንስሳት እንክብካቤ ቡድን እንዳስታወቀው በኬንያ የአምቦሴል ብሄራዊ ፓርክ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁና በርካታ ዝሆኖች የሚገኙበት ፓርክ ሲሆን በሀገሪቷ ካሉት 34 ሺህ 800 ዝሆኖች ውስጥ ብዙዎቹ የሚገኙት በዚሁ ፓርክ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም የሰዎች ቁጥር መጨመር እና በፓርኩ ዙሪያ የሚደረገው ሰፈራ መስፋፋት ደግሞ ለሠዎችና ዝሆኖች ግጭት ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

አብዛኛዎቹ ሰዎች የሞቱት ደግሞ በዚሁ ፓርክ አካባቢ በሚኖሩ ዝሆኖችና ሰዎች መካከል እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

በዚህም ሰዎች ብቻም ሳይሆኑ በአመቱ 7 የሚሆኑ ዝሆኖች ደግሞ በሰዎች መገደላቸውም ተነግሯል ሲል አልጄዚራ አግቧል፡፡

በጅብሪል ሙሀመድ
ሕዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *