የእንሰት አዘገጃጀትን የሚያዘምን ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ሊገባ ነው

የተፈጠረው የእንሰት ማዘጋጃ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተለይ የሴቶችን ጫና ከመቀነስና እንሰቱን በሚፍቁበት ወቅት ከሚያጋጥማቸው የጽንስ መቋረጥና የጀርባ ህመም እንደሚታደግ ታምኖበታል፡፡

የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ደረጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የእንሰት አዘገጃጀትን የሚያዘምን ቴክኖሎጂ ሰርቷል ብለዋል

እንደሚታወቀው ቆጮ(እንሰት) የሚፋቀው በባህላዊ መንገድ እግር ተሰቅሎ ነው ይሄን አድካሚ ሂደትም ይቀንሳል ተብሏል፡፡ ቆጮው ከተፋቀ በኋላም የመጭመቅ ሂደቱን የሚከውን መሳሪያም ተመራማሪዎቹ እንደፈጠሩ ሰምተናል፡፡

ቴክኖሎጂው በባህላዊ መንገድ ከሚዘጋጀው ቆጮ 45በመቶ ያህል ብክነትን ይከላከላል የሚሉት የኢንስቲቲዩቱ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ደረጀ ማሽኑ ጊዜ ቆጣቢ ስለመሆኑም ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም በባህላዊ መንገድ ሲዘጋጅ 15ሰው ሆነው በአንድ ቀን ሊጨርሱት የሚችሉትን የቆጮ መፋቅ ስራ ቴክኖሎጂው ወደ 2ሰአት ያወርድላቸዋል ብለዋል፡፡

የእንሰት አዘገጃጀት ቴክኖሎጂውን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋርም ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ አቶ ፍሬው ደረጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እንሰትን በደቡብ እና ደቡብ ምእራብ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ከ20 ሚሊዬን በላይ ዜጎች ለምግብነት እንደሚያውሉት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ

ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.