ሴቶች በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ።

ኮሚሽኑ ከምርጫ ጋር በተያያዘ በሴቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን በተመለከተ፣ የተለዩ ችግሮችን ለማሳወቅና ወደፊት የሚሰተካከሉበትን መፍትሄ ለመፈለግ ሲባል ከሚመለከታቸው አካለት ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ኪሚሽነር ወ/ሮ መሰረት ማሞ እንዳሉት፣እስካሁን ድረስ በምርጫ ሂደት ወቅት ከተለዩት ችግሮች ውስጥ፣ በተመራጭ ሴቶች ላይ የደረሱ አካላዊ ጥቃቶች፣ የግድያ ሙከራ ማደረግ፣ ከምርጫ እራሳቸውን እንዲያገሉ ማሰፈራራት፣ በባህልም ይሁን በሃይማኖት ሴቶች እንዳይመርጡ ወይም እንዳይመረጡ መከልከል ዋናዎቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ወ/ሮ መሰርት ባለፉት የምርጫ ሂደት ላይ በተለይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች የምርጫ ተሳትፎ በ1987 ዓ.ም 2 በመቶ ከነበረው በ2007 ዓ.ም ወደ 38.8 በመቶ ከፍ እንዳለ ተናግረዋል። እንዲሁም በሀገራችን በቅርቡ በተደረገው ሪፎርም በካቢኔ ደረጃ 47.6 በመቶ የሴቶች ተሳተፎ ከፍ ማለቱንም አድንቀዋል።

ኮሚሽነሯ እንደሚሉት ከሆነም፣ ምንም እንኳን ይሄው የሴቶች ውሳኔ ሰጭነት አበረታች ቢሆንም፣ አሁንም በሴቶች ላይ በምርጫ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያና በማናቸውም መንገድ በመጠቀም በአካልና ስነ ልቦና ላይ ጫና የሚያሳድሩት ችግሮች ደግሞ፣ ሴቶች እጩ ተመራጭና መራጮች፣ ታዛቢዎችና አስተባባሪዎች እንዳይሆኑ የሚያድርጉ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ይህም ሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውንም ሆነ የዜግነት መብታቸውን የሚገድብ በመሆኑ፣ ሊስተካከል ይገበዋል ብለዋል።እነዚህ ችግሮች የሚፈቱት ደግሞ በራሳቸው በሴቶች ተሳትፎ ጭምር በመሆኑ ሴቶች በፖለቲካ ያላቸውን ተሳትፎ ማጠናከር፣የምርጫ ድምጻቸውን ለማን እንደሚሰጡ ቀድሞ በእውቀት እና መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ማስተላለፍ ሲቻል ነው ብለዋል።

በመሆኑም አስፈጻሚ አካላት ከግማሽ በመቶ በሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ድርሻ ያላቸው ሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲጎለብት ሁሉም አጀንዳ እንዲያደርገው ወይዘሮ የሺሀረግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ጅብሪል ሙሃመድ
ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *