ዳሽን ባንክ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የዳሽን ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለ አክሲዮኖች 27ተኛ መደበኛ ጉባኤ እና 24ተኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ መቻሬ ሜዳ እካካሄደ ነው።

ባንኩ በዚህ ጊዜ እንዳስታወቀው እየተጠናቀቀ ባለው 2019/20 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ያተረፈ ሲሆን የተገኘው ትርፍ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 40 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

በበጀት አመቱ 8 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ያለው ሲሆን አጠቃላዩ ደግሞ 53.8 ቢሊየን ነው ሲሉ የባንኩን አመታዊ ሪፖርት ያቀረቡት የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ነዋይ በየነ ገልጸዋል።

ባንኩ በተጠናቀቀው ዓመት 2 ከወለድ ነጻ ቅርንጫፎችን እና 10 ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ከፍቷል።

በአሁኑ ሰአትም አጠቃላይ የዳሽን ባንክ የቅርንጫፍ ብዛት 423 መድረሱ ተነግሯል።

በአጠቃላይ የአሞሌ የሞባይል መተግበሪያን የሚጠቀሙ ደንበኞቼ ቁጥር 1 ሚሊየን 983ሺ ደርሰዋል ብሏል ዳሽን ባንክ።

ባንኩ 17 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር እንደሰጠም በአመታዊ ሪፖርቱ ቀርቧል።

የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ከአቅም ጋር አለመጣጣም ዘርፉ ላይ እንቅፋት ሆኗል ሲሉ አቶ ነዋይ በየነ ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በመቅደላዊት ደረጀ
ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *