የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለወባ በሽታ ምርመራ የሚውሉ 493 ማይክሮስኮፖችን አሰራጨ።

ኤጀንሲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ከታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ 493 የወባ በሽታ መመርመሪያ ማይክሮስኮፒዎችን ለመንግስት የጤና ተቋማት አሰራጭቷል።

እነዚህ የወባ ህክምና መሳሪያዎችም ለኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ፣ሶማሌ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ለጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮዎች ተሰራጭተዋል ተብሏል።

እነዚህ የወባ በሽታ መመርመሪያ መሳሪያዎች ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸው ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *