የዶክተር ጥላሁን ገሰሰ አዲስ አልበም በቅርቡ ለአድማጭ እንደሚቀርብ ተገለጸ።

የአርቲስት ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ በቅርቡ እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡

ለአድማጭ የሚቀርበው አልበም ጥላሁን ገሰሰ በህይወት እያለ የሰራቸው ነገር ግን ለአድማጭ ያልቀረቡ ስራዎች ናቸው ተብሏል፡፡

የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን በዙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳረጋገጡት ከዚህ በፊት ለአድማጭ ያልቀረቡ እና ያልታተሙ ስራዎች በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም አልበሙ ምን ያህል ሙዚቃዎች እንዳካተተ እና የአልበሙ ይዘት በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን ብለውናል ወ/ሮ ሮማን፡፡

አሁን ላይ ካሳታሚ ድርጅቶች እና የአልበሙን ስራ ከሚከታተሉ ሰዎች ጋር በአልበሙ ዙርያ ምክክር እያደረግን እንገኛለንም ብለዋል፡፡

አዲስ በሚታተመው የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አልበም በመድረክ የተጫወታቸው ነገር ግን ህዝቡ የማያውቃቸው ስራዎች እንዳሉበትም ነው የተነገረው፡፡

አልበሙን ያቀናበረው አበጋዝ ክብረወርቅ ሽኦታ መሆኑንም ወይዘሮ ሮማን ነግረውናል።

የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አድናቂዎች በተለያዩ ጊዜያቶች የአልበሙ ሂደት ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡

በመጨረሻም የአልበሙ መታተም እውን የሆነ መስሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *